Home 🎬 Bollywood 🎵 Pakistani 🎤 English Pop

Wiste Weyira

👤 Michael Belayneh • 🎼 And Qal [@Ethopian_New_Music] • ⏱️ 5:31
🎵 1654 characters
⏱️ 5:31 duration
🆔 ID: 12189033

📜 Lyrics

ካይምሮዬ ጓዳ ቃላት ለቃቅሜ
ከልቤ ማሳ ላይ ስሜቴን ቃርሜ
ብሞክር ልስልሽ ባምጥሽ ባምጥሽ
ስም አልባ ሆነብኝ ረቂቅ ውበትሽ

ረቂቅ ውበትሽ የልብ ያይኔ አዋጅ
የማነሽ እኩያው የማነሽ ተጣማጅ
እንቡጥ ጽጌረዳ የመስከረም አደይ
የተስፋ ማለዳው ልጅነት የጸደይ

የዘመን ጌጥ ነሽ ወይ አምሳለ ሰው ዕንቁ
ሲያይሽ የሚጠግብ የሕዝብ አዳም ስንቁ
በሚመጥንሽ ቃል በሚመስልሽ ቀለም
ተክኖ በጥበብ የሚገልፅሽ የለም

ካይምሮዬ ጓዳ ቃላት ለቃቅሜ
ከልቤ ማሳ ላይ ስሜቴን ቃርሜ
ብሞክር ልስልሽ ባምጥሽ ባምጥሽ
መልክ አልባ ሆነብኝ ረቂቅ ውበትሽ

የማታ ጀምበር ነሽ የሕይወት አመሻሽ
ዓለም በቃኝ ያለሽ ጽድቅ መዳረሻሽ
ወይን ጠጅ ነሽ ወይ የጣዕም መናኔ
እንዴት የ'ጣሽ ክፋይ አልገባ አልሽኝ እኔ

ቸገረኝ ከበደኝ ልገልፅሽ አልቻልኩም
አንቺማ ረቂቅ ነሽ እኔ አልጎበዝኩም
የማነሽ ቅኔ-ሰብ የማነሽ ምስጢር
ስንቱ ራሱን ጥሏል ሊያገኝሽ ሲጥር
የማነሽ ትንሣኤ የማነሽ መከራ
ውስጥሽ ጸባይሽ ፍፁም ውስጠ ወይራ
ሸማሽ ያገር ባህል ዘርፉ የባንዲራ
ሙዳየ ቃልኪዳን የእግዜር ድንቅ ሥራ

የእግዜር እፁብ ሥራ
የእግዜር እፁብ ሥራ
እፁብ ድንቅ ሥራ
እፁብ ድንቅ ሥራ

⏱️ Synced Lyrics

[00:25.90] ካይምሮዬ ጓዳ ቃላት ለቃቅሜ
[00:31.93]
[00:37.16] ከልቤ ማሳ ላይ ስሜቴን ቃርሜ
[00:44.04]
[00:48.74] ብሞክር ልስልሽ ባምጥሽ ባምጥሽ
[00:56.03]
[00:59.35] ስም አልባ ሆነብኝ ረቂቅ ውበትሽ
[01:06.96]
[01:10.87] ረቂቅ ውበትሽ የልብ ያይኔ አዋጅ
[01:19.04]
[01:22.47] የማነሽ እኩያው የማነሽ ተጣማጅ
[01:29.05]
[01:33.44] እንቡጥ ጽጌረዳ የመስከረም አደይ
[01:41.95]
[01:44.67] የተስፋ ማለዳው ልጅነት የጸደይ
[01:53.05]
[01:56.37] የዘመን ጌጥ ነሽ ወይ አምሳለ ሰው ዕንቁ
[02:03.05]
[02:06.18] ሲያይሽ የሚጠግብ የሕዝብ አዳም ስንቁ
[02:14.09]
[02:18.94] በሚመጥንሽ ቃል በሚመስልሽ ቀለም
[02:26.02]
[02:29.93] ተክኖ በጥበብ የሚገልፅሽ የለም
[02:37.29]
[02:52.68] ካይምሮዬ ጓዳ ቃላት ለቃቅሜ
[03:00.00]
[03:04.16] ከልቤ ማሳ ላይ ስሜቴን ቃርሜ
[03:11.05]
[03:15.42] ብሞክር ልስልሽ ባምጥሽ ባምጥሽ
[03:21.99]
[03:26.47] መልክ አልባ ሆነብኝ ረቂቅ ውበትሽ
[03:33.98]
[03:38.12] የማታ ጀምበር ነሽ የሕይወት አመሻሽ
[03:44.97]
[03:49.36] ዓለም በቃኝ ያለሽ ጽድቅ መዳረሻሽ
[03:57.06]
[04:00.60] ወይን ጠጅ ነሽ ወይ የጣዕም መናኔ
[04:06.94]
[04:12.07] እንዴት የ'ጣሽ ክፋይ አልገባ አልሽኝ እኔ
[04:18.99]
[04:23.03] ቸገረኝ ከበደኝ ልገልፅሽ አልቻልኩም
[04:28.26] አንቺማ ረቂቅ ነሽ እኔ አልጎበዝኩም
[04:33.56] የማነሽ ቅኔ-ሰብ የማነሽ ምስጢር
[04:39.61] ስንቱ ራሱን ጥሏል ሊያገኝሽ ሲጥር
[04:45.70] የማነሽ ትንሣኤ የማነሽ መከራ
[04:50.84] ውስጥሽ ጸባይሽ ፍፁም ውስጠ ወይራ
[04:56.42] ሸማሽ ያገር ባህል ዘርፉ የባንዲራ
[05:01.77] ሙዳየ ቃልኪዳን የእግዜር ድንቅ ሥራ
[05:07.63] የእግዜር እፁብ ሥራ
[05:11.53] የእግዜር እፁብ ሥራ
[05:13.34] እፁብ ድንቅ ሥራ
[05:16.33] እፁብ ድንቅ ሥራ
[05:18.12]

⭐ Rate These Lyrics

☆☆☆☆☆
Average: 0.0/5 • 0 ratings