Home 🎬 Bollywood 🎵 Pakistani 🎤 English Pop

Tsion - Dengle Mariam

👤 Gebre Yohannes • 🎼 Ethiopian Orthodox Mezmur • ⏱️ 6:16
🎵 1695 characters
⏱️ 6:16 duration
🆔 ID: 14823082

📜 Lyrics

ከሰማዩ ከፍታ ከፍብላ ፅዬን፣
በሰገነት ላይ ተቀምጣ፣
ድንግል በክብር በግርማ ትኖራለች አጊጣ።(፪)

አይን ከሞላባቸው ከኪሩቤል፣

ክንፋቸው ከበዛ ከሱራፌል።
ከሊቃናቱ ሁሉ ትበልጣለች፣
እሳተ መለኮት በሆዱዋ ስለተሸከመች።

ከሰማዩ ከፍታ ከፍብላ ፅዬን፣
በሰገነት ላይ ተቀምጣ፣
ድንግል በክብር በግርማ ትኖራለች አጊጣ።(፪)

ከንጉሱ በስተቀኝ ከዙፋኑ፣
ንግስቲቱ ትቆማለች በየቀኑ።
የቃል ኪዳን ቀሚሱአን ተጐናፅፉ፣
የምትማልድልን ድንግልናት የሁላችን ተስፉ።

ከሰማዩ ከፍታ ከፍብላ ፅዬን፣
በሰገነት ላይ ተቀምጣ፣
ድንግል በክብር በግርማ ትኖራለች አጊጣ።(፪)

በብርሀን ወንበር ላይ ተቀምጣለች፣ ጨርቃን
ከእግሩአ በታች ተጫምታለች፡፡
የቅድስናን ውበት ተሸልማ፣

የምታብረቀርቀው እሱናት የልኡል ከተማ፡፡

ከሰማዩ ከፍታ ከፍብላ ፅዬን፣
በሰገነት ላይ ተቀምጣ፣
ድንግል በክብር በግርማ ትኖራለች አጊጣ።(፪)

ከእብራውያን ሴቶች ተለይታ፣

ከሄዋን ዘሮች ሁሉ ታየች ጐልታ።
ሰባቱን መቅረዝ ልጅአ ያበራል፣

ስጋዋን ተዋህዶ በፍቅር እኛኑ መስሉአል።

ከሰማዩ ከፍታ ከፍብላ ፅዬን፣

በሰገነት ላይ ተቀምጣ፣
ድንግል በክብር በግርማ ትኖራለች አጊጣ።(፪)

⭐ Rate These Lyrics

☆☆☆☆☆
Average: 0.0/5 • 0 ratings